አትሌት ደራርቱ ቱሉ ፌዴሬሽኑን በጊዜያዊነት እንድትመራ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ወስኗል

61
አዲስ አበባ ህዳር 6/2011 ኮለኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በጊዜዊነት እንድትምራ የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ወሰነ። ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን ለአራት ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ለመምራት በ2009 ዓ.ም ጥቅምት ወር በተካሄደው 20ኛው ጠቅላላ ጉባዔ መመረጡ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ኃይሌ ሁለት ዓመታትን ከመራ በኋላ ቀሪ ሁለት ዓመታት እየቀሩት ህዳር 2 ቀን 2011 ዓ.ም በራሱ ፍቃድ ስልጣን መልቀቁ ይታወቃል። ይህን ተክትሎም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ትናንት አመሻሽ ባደረገው አስቸኳይ ስብስባ የፌዴሬሽኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት ደራርቱ ቱሉ ጠቅላላ ጉባኤው እስኪካሄድ ድረስ ፌዴሬሽኑን እንድትመራ ወስኗል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እስከ ሁለት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ አስቸኳይ ጠቅለላ ጉባኤውን በመጥራት ፕሬዚዳንት እንደሚሾም ይጠበቃል።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም