የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአምባሳደሮች ሽግሽግ አደረገ

119
አዲስ አበባ ግንቦት 15/2010 የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአምባሳደሮች ጥሪ እና ሽግሽግ አደረገ። በዚህም መሰረት አምባሳደር አሚን አብዱልቃድር ከሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ወደ አልጄሪያ ተዛውረው ባለ-ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው እንዲሰሩ ተመድበዋል። አምባሳደር ውብሸት ደምሴ በሳዑዲ አረቢያ ጅዳ ከሚገኘው ቆንስላ ጸህፈት ቤት አዲስ አበባ ወደሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት ተጠርተዋል። በአልጄሪያ ባለ-ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አምባሳደር ሰለሞን አበበ በተመሳሳይ ኃላፊነት ወደ ናይጄሪያ እንዲዛወሩ ተደርጓል። በተመሳሳይ አምባሳደር ግሩም አባይ ከሩስያ ሞስኮ ወደ ቤልጂየም ብራሰልስ፣ አምባሳደር አብዱላዚዝ አህመድ ከኩዌት ወደ ሳውዲ አረቢያ ሪያድ ተዛውረዋል። ሽግሽጉ መንግስት ከአገሮቹ ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከርን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኢዜአ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም