የሰሞኑ የመንግስት እርምጃ ወንጀል ሰርቶ ከህግ ማምለጥ እንደማይቻል ያረጋገጠ ነው-የአዲስ አበባ ነዋሪዎች

235
አዲስ አበባ ህዳር 4/2011 በከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የህዝብን ንብረት ለግል ጥቅም አውሎ ከህግ ተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይቻል የሚያረጋግጥ እርምጃ መንግስት መውሰዱ ተገቢ መሆኑን አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የሰጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ። የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ትናንት የሰጠውን መግለጫ ተከትሎ በሙስና ወንጀልና በሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት ወስጥ የቀድሞው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ በርካታ ሰዎች እንደሚገኙበት ይታቃል። የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም መንግስት በክትትልና በመረጃ በማስደገፍ ተጠርጣሪ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ተገቢ ስለመሆኑም ነው የተናገሩት። አቶ መንግስቱ ታደሰ እንደተናገሩት እንደዚህ አይነት ችግሮች እንዳሉ በወሬ ደረጃ በጭምጭምታ እንሰማ ነበር፣ ነገር ግን በዚህ መልኩ ይሆናል ብለን አልጠበቅንም። አገሪቷ ከድህነት አረንቋ ለመላቀቅ እየኳተነች ባለችበት በዚህ ወቅት እንዲህ አይነቱ የወንጀል ድርጊት መፈጸሙ እጅግ የሚያሳፍር ነውም ብለዋል። በሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ የተደረገውም ድርጊት "ከጠላት እንኳን የማይጠበቅ ነው" ያሉት ከገንዘቡም በላይ እጅግ የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ እጅግ የከፋ ነበር ያሉት አቶ መንግስቱ ፣ እነዚህ ግለሰቦች  ለፍርድ በመቅረባቸው ደስተኛ ነኝም ብለዋል። አቶ ሲሳይ ተፈራ በበኩላቸው “እርምጃው ትክክለኛና ተገቢ ነው፤ እነዚህ ሰዎች እኛ የቀን ስራ እየሰራን ኢትዮጵያውያን እነሱ በቤታቸው እውነት ለመናገረ ሊፈርሱ የደረሱ ነበረ” ነው ያሉት፡፡ ወይዘሮ እመቤት ከበደ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ የተደረገውም ድርጊት "ከጠላት እንኳን የማይጠበቅ ነው" ያሉት ብለው ይህን የፈጸሙት አካላት ለህግ መቅረባቸው ተገቢና ሌሎችንም የሚያስተምር ጭምር ነው በማለት ገልጸዋል። “ በአሁኑ ሰዓት በመሰረቱ  የተፈጸሙት ግፎች በተለይ ጠቅላይ አቃቤ ህጉ የገለጿቸው ነገሮች በእውነት በእውነት የሰው ልጅ ሆኖ ሰው ላይ እሄንን ይፈጽማል ለማለት በጣም ይከብዳል፤ ከአዕምሮ በላይ ነው” ያሉት ደግሞ አቶ ተገኝ ባዩ ናቸው፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ኮርፖሬሽኑ ከ2004-2010 ዓ.ም ድረስ ከ37 ቢሊዮን ብር በላይ የውጭ አገር ግዥ ያለጨረታ መፈጸሙን ትናንት መግለጹ ይታወቃል። ኮርፖሬሽኑ የመንግሥት አስራርና ሕግ በመተላለፍ ትላልቅ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ግዥዎችን ሲፈጽም ቆይቷል። ከሙሲና ወንጀል በተጨማሪ ባለፉት ዓመታት በሽብርተኝነትና ተያያዥ ወንጀሎች በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲፈጽሙ የነበሩ በርካታ ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም