ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ በቁጥጥር ስር የዋሉ የሙስና ወንጀል ተጠርጣሪዎችን ይፋ አደረገ

98
አዲስ አበባ ህዳር 4/2011 የፌዴራሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦችን ዝርዝር ይፋ አደረገ።
  1. ብርጋዴር ጄኔራል ጠና ቁርንዴ ኢጄታ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የማርኬቲንግ ኃላፊ
  2. ብርጋዴር ጄኔራል ብርሃ በየነ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ኦዲትና ኢንስፔክሽን ኃላፊ
  3. ብርጋዴር ጄኔራል ጥጋቡ ፈትላ መረሳ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የኮርፖሬት ሎጂስቲክስና ሰፕላይ ኃላፊ
  4. ብርጋዴር ጀኔራል ሃድጉ ገብረጊወርጊስ ገብረስላሴ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የኮርፖሬት ኒው ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ኃላፊ
  5. ኮሎኔል ሸጋው ሙሉጌታ ተስፋሁን - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የወታደራዊ ምርቶች ኦፕሬሽን ኃላፊ
  6. ኮሎኔል ሙሉ ወልደገብርዔል ገብረእግዛብሄር - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የኒው ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ኃላፊ የነበሩ
  7. ኮሎኔል ዙፋን በርሄ ይህደግላ - የመከላከያ ጤና ኮሌጅ ሰራተኛ
  8. ሌተናል ኮሎኔል አስምረት ኪዳኔ አብርሃ - የጋፋት አርማመንት ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ተወካይ ኃላፊ የነበሩ
  9. ኮሎኔል አለሙ ሽመልስ ብርሃን - በብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን በኮርፖሬት ሎጂስቲክስና ሰፕላይ የትራንስፖርት ኃላፊ
  10. ኮሎኔል ያሬድ ሃይሉ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኮርፖሬት ኒው ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት የፕሮጀክት ኃላፊ
  11. ኮሎኔል ተከስተ ሀይለማሪያም አድሃኑ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የኒው ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ኃላፊ የነበሩ
  12. ኮሎኔል አዜብ ታደሰ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኮርፖሬት ማርኬቲንግ የሽያጭ ኃላፊ
  13. ሻለቃ ሰመረ ሀይሌ ሀጎስ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በደጀን አቪዬሽን የኢንዱስትሪ ኦፕሬሽን ኃላፊ
  14. ሻምበል ይኩኖአምላክ ተስፋዬ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኮርፖሬት ማርኬቲንግና ሽያጭ የፕሮሞሽን ኃላፊ
  15. ኮሎኔል ደሴ ዘለቀ ብርሃን - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የአዳማ እርሻ ስራዎች ኢንዱስትሪ ስራ አስኪያጅ
  16. ሌተናል ኮሎኔል ሰለሞን በርሄ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በብረታ ብረት ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ የፋይናንስ ኃላፊ
  17. ሻለቃ ይርጋ አብርሃ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በህብረት ማሽን ቢዩልዲንግ ኢንዱስትሪ የፋይናንስ ኃላፊ
  18. ኮሎኔል ግርማይ ታረቀኝ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኮርፖሬት ሎጂስቲክስና ሰፕላይ የንብረት አስተዳደር ኃላፊ
  19. ሻምበል ገብረስላሴ ገብረጊዮርጊስ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ትራንስፎርሜሽን የአቅም ግንባታ ማዕከል ኃላፊ
  20. ሻምበል ሰለሞን አብርሃ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኮርፖሬት ትራንስፎርሜሽን የስልጠና ኃላፊ
  21. ሻለቃ ጌታቸው ገብረ ስላሴ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የደን ምንጣሮ ክትትል ኃላፊ
  22. ሌተናል ኮሎኔል ይሰሃቅ ሀይለማሪያም አድሃኖም - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኮርፖሬት ኮሜርሻልና ሲቪል ምርቶች ኦፕሬሽን የፕላኒንግና ኮንትሮል ኃላፊ
  23. ሻለቃ ክንደያ ግርማይ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የፋይናንስ ኃላፊ
  24. ሌተናል ኮሎኔል አዳነ አገርነው - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኮርፖሬት ሎጂስቲክስና ሰፕላይ የንብረት ክፍል ኃላፊ
  25. ሻለቃ ጌታቸው አጽብሃ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ኢንፍራስትራክችርና ኮርፖሬሽን ማሽነሪ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኦፕሬሽን ኃላፊ
  26. ቸርነት ዳና - የዋይ ቲ ኦ ኩባንያ ባለቤትና ከብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አመራሮች ጋር የጥቅም ትስስር የነበራቸው ደላላ
  27. አያልነሽ መኮንን አራጌ - ማስረጃ ልታጠፋ ስትል በቁጥጥር ስር የዋለች መሆናቸውን የፌዴራሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አስታውቋል።
 
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም