የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ ተጠናቀቀ

2420

አዲስ አበባ ጥቅምት 29/2011 በ14 ሺህ 500 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ ሙሉ ለሙሉ መጠናቀቁን የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ኢብራሂም ኡስማን ተናገሩ።

የኢንዱስትሪ ፓርኩ ከአንድ ወር በኋላ ይመረቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም በድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል።

ኢንዱስትሪ ፓርኩ አንድ ከተማ ሊኖረው የሚገባውን መሰረተ ልማትና ሌሎችን ያካተተ ነው።

በ51 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባው የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የመጀመሪያ ምዕራፍ 15 ሼዶች ያሉት ሲሆን ከ40 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከድሬዳዋ ከተማ 14 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ነው።

በድሬዳዋ የተካሄደውን የሰላም ኮንፈረንስ መጠናቀቅ ተከትሎ የአስተዳደሩን የልማት ስራዎች ተዘዋውረው የጎበኙት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ኬሪያ የኢንዱስትሪ ፓርክ፣ የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበርንና የድሬዳዋ ሚሌኒየም ፓርክን ጎብኝተዋል።