ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ጎንደር ከተማ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ጎንደር ከተማ ገቡ
108
አዲስ አበባ ጥቅምት 29/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኤርትራውን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለመቀበል ዛሬ ከሰዓት ጎንደር ከተማ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎንደር አፄ ፋሲል አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። የኤርትራውን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአማራ ክልል ጎንደርና ባህር ዳር ጉብኝት ለማድረግ ነገ ጎንደር ሲገቡ አቀባበል ለማድረግ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ዛሬ ማምሻቸውን በጎንደርና አካባቢዋ ካሉ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችና የአገር ሽማግሌዎች ጋር በአካባቢው በተከሰቱ ግጭቶች ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ። ባለፈው ነሐሴ ወር በአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ የተመራ ልዑክ በአስመራ ጉብኝት ማድረጉና በወቅቱ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አማራ ክልልን እንዲጎበኙ የቀረበላቸውን ጥያቄ መቀበላቸው ይታወሳል።