ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጎንደርን ሊጎበኙ ነው

54
ጎንደር ጥቅምት 28/2011 የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከነገ በስቲያ ጎንደር ከተማን እንደሚጎበኙ የከተማ አስተዳደሩ ኮሙዩኒክሽን መምሪያ አስታወቀ፡፡ የመምሪያው ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ሞገስ ለኢዜአ እንደተናገሩት ፕሬዚዳንቱ በታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ የሚያደርጉት ጉብኝት ለአንድ ቀን የሚቆይ ነው፡፡ ፕሬዚዳንቱ በጉብኝታቸው የከተማዋን የልማት እንቅስቃሴዎችና ታሪካዊ ሥፍራዎችን ተዘዋውረው ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። የከተማዋ ነዋሪዎች፣ አባት አርበኞችና የከተማዋ አስተዳደር አመራሮች ከአጼ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ ጀምሮ ለፕሬዚዳንቱ ደማቅ አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት ማድረጋቸውንም ኃላፊው ጨምረው ገልጸዋል ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም