በነቀምቴ ከተማ ዐብያተ ክርስቲያንና ምዕመናን የጽዳት ዘመቻ አካሄዱ

62
ነቀምቴ ጥቅምት 26/2011 በነቀምቴ ከተማ ዐብያተ ክርስቲያንና ምዕመናን ትናንት የጽዳት ዘመቻ አካሄዱ። ከተማዋን ጽዱና ማራኪ ለማድረግ በዋና ዋና መንገዶች ላይ በተካሄደው ዘመቻ ላይ 22 ዐብያተ ክርስቲያንና 25 ሺህ የሚሆኑ ምዕመናን ተካፍለዋል። ከጽዳት ዘመቻው ተሳታፊዎች መካከል የምዕራብ ኢትዮጵያ ዐብያተ ክርስቲያን ፀሐፊ ፓስተር አምብሳ ታስሳ እንደተናገሩት የከተማዋን ንጽህና መጠበቅና ለኑሮ  ምቹ እንድትሆን ማድረግ  ከሁሉም አካላት ይጠበቃል። በመሆኑም ጽዳት ከራስና ከአካባቢ ስለሚጀምር ምዕመናንና የከተማዋን ነዋሪዎች ያሳተፈ ዘመቻ መካሄዱን ገልጸዋል። የሙሉ ወንገል ቤተክርስትያን አገልጋይ ፓስተር ታዬ ተስፋዬ በበኩላቸው በከተማው ጽዳት ላይ እንዲነሱ የተነሳሱት ከግንባታ ጋር በተያየዘ በየአካባቢው የሚጣለውን ቆሻሻ ለማስወገድና  ለአካባቢው ሕዝብ ምሳሌ ለመሆን ነው ብለዋል። ምዕመናንን በጽዳቱ ሥራ ላይ በማሳተፍ ከተማው ውብ እንድትሆን የጀመሩትን ሥራ እንደሚቀጥሉበት አስታውቀዋል። በነቀምቴ ከተማ አስተዳደር የከተማ ጽዳት ቡድን መሪ አቶ ተስፋዬ ደሬሳ በከተማው በሚገኙ ዐብያተ ክርስቲያን የተከናወነው የጽዳት ዘመቻ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ጉልበት ፈሶበታል ብለዋል። አቶ ተስፋዬ እንደሚሉት ዘመቻው በከተማዋ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል በር ከፋች መሆኑን ተናግረዋል። ከተማውን ጽዱ ውብና አረንጓዴ ማድረግ ከሁሉም ባለድርሻ አካላትና ስለሚጠበቅ ተሳትፎአቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም