ባህርዳር ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን በማሸነፍ የውድድር ዓመቱን በድል ጀምሯል - ኢዜአ አማርኛ
ባህርዳር ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን በማሸነፍ የውድድር ዓመቱን በድል ጀምሯል
112
አዲስ አበባ ጥቅምት 25/2011 በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ባህር ዳር ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ። ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ባህር ዳር ከተማ በ56ኛው ደቂቃ ወሰኑ ዓሊ ባስቆጠረው ጎል ማሸነፍ ችሏል። በጨዋታው ግርማ ዲሳሳና አስናቀ ሞገስ ከባህር ዳር ከተማ ቢጫ ካርድ የተመለከቱ ሲሆን፤ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ሄኖክ አዱኛ ብጫ ካርድ አይቷል። ክልል ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ቡና ደደቢትን 2ለ0፣ ፋሲል ከተማ ሀዋሳ ከተማን 3ለ1፣ እንደዚሁም መከላከያ አዲስ አዳጊውን ደቡብ ፖሊስን 2ለ1 አሸንፈዋል። በፕሪሚየር ሊጉ ቀሪ የ2ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሚቀጥለው ሳምንት ይካሄዳሉ።