በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ተከስቶ የነበረው ረብሻ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ

65
ሚዛን ግንቦት 15/2010 በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲና አካባቢው ተከስቶ የነበረውን ረብሻ መቆጣጠር መቻሉን የካፋና ቤንች ማጂ ዞኖች ኮማንድ ፖስት አስታወቀ፡፡ የኮማንድ ፖስቱ ሰብሳቢ ኮሎኔል ፀጋዬ አብርሃ ለኢዜአ እንደገለጹት ግጭቱ ትናንት የተከሰተው ሴት ተማሪዎች በተደጋጋሚ ፆታዊ ትንኮሳ እንደሚደርስባቸው ለዩኒቨርሲቲው አመልክተው  ምላሽ ባለማግኘታቸው ነው፡፡ ይህን ተከትሎም የተወሰኑ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው እና  ከግቢው ወጥተውም ወደ ሚዛን አማን ከተማ በማምራትና ረብሻ በማስነሳት በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል፡፡ በአካባቢው የተሰማሩት የህግ አስከባሪዎች ከህብረተሰቡ ጋር ባደረጉት ጥረት በአሁኑ ወቅት ረብሻውን መቆጣጠርና አካባቢውንም ማረጋጋት መቻሉን ኮሎኔል ፀጋዬ አስታውቀዋል፡፡ በቀጣይም ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር በመወያየት ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት እንደሚሰራም ነው የገለጹት፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም