የአማራ ክልል ምክርቤት አዳዲስ ሹመቶችን አጸደቀ - ኢዜአ አማርኛ
የአማራ ክልል ምክርቤት አዳዲስ ሹመቶችን አጸደቀ
96
ባህር ዳር ጥር 24/2011 የአማራ ክልል ምክርቤት 11ኛ መደበኛ ጉባኤ ለምክትል ርዕሰ መስተዳደርና ለቢሮ ሃላፊዎች አዳዲስ ሹመቶችን አጸደቀ። በክልሉ ርዕሰ-መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አቅራቢነት አቶ ላቀ አያሌውን ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር፣ አቶ ንጉሱ ጥላሁንን በምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ማዕረግ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ በማድረግ ሹሟል። እንዲሁም አቶ መላኩ አለበል በምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ማዕረግ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ልማት ቢሮ ኃላፊ አድርጎ ሾሟ። ምክር ቤቱ ለሌሎች ኃላፊነቶችም የቀረበውን ሹመት መርምሮ አፅድቋል፡፡በዚህም መሰረት፦
- ዶክተር ቦሰና ተገኘ የግብርና ቢሮ ኃላፊ
- የቴክኒክ፣ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ -አቶ ሻምበል ከበደ
- የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ -ወይዘሮ ብዙአየሁ ቢያዝን
- የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት- አቶ ፍርዴ ቸሩ
- የሰላም ግንባታና የህዝብ ደህንነት ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ -ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ
- የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ -ወይዘሮ አስናቁ ድረስ
- የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ - ዶክተር ሙሉነሽ አበበ በማድረግ የሾመ ሲሆን 4 የጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ 5 የከፍተኛ ፍርድ ቤት፣6 የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመትም አጽድቋል፡፡