በደቡብ ክልል ምክር ቤት የተዋቀሩ ሦስት ዞኖችና 44 ወረዳዎች ዝርዝር

280
ሐዋሳ ጥቅምት 23/2011 የደቡብ ክልል ምክር ቤት በአምስተኛ ዙር አራተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ስምንተኛ መደበኛ ጉባዔው በዋናነት በህዝብ ሲነሱ የነበሩ ጥያቄዎችን መሠረት በማድረግ ሶስት ዞኖችንና 44 ወረዳዎችን በአዲስ መልክ እንዲደራጁ ወስኗል፡፡ ምክር ቤቱ ባስቀመጣቸው የህዝብ ቁጥር፣ የመሬት ስፋትና መልክዓ ምድራዊ ሁኔታ መስፈርት ለቀበሌ አምስት ሺህ ህዝብ ለወረዳ 100 ሺህ ህዝብ መነሻ ሆነዋል። በዞን ደረጃ ለመዋቀር እያንዳንዳቸው 100 ሺህ ህዝብ ያላቸው ቢያንስ ሶስት ወረዳዎችን በማሟላታቸው ኮንሶ፣ ሀላባና ጎፋ ዞን እንዲሆኑ ፈቅዷል፡፡ አዲሶቹ ዞኖች የዞን ማዕከልና የዞኑን መጠሪያ ከህዝብ ጋር በሚደረግ ውይይትና በህዝብ አመኔታ መሠረት እንዲሰጣቸው መደረግ እንዳለበት ተገልጿል፡፡ የቀድሞዎቹ የጋሞጎፋና የሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን ላይ የጎፋ ዞንና የኮንሶ ዞን በአዲስ መልክ እንዲደራጁ በመደረጉ የቅርጽ ለውጥ አምጥተዋል፡፡ ከዚህ ባለፈ አዲስ የወረዳ መዋቅር የተሰጣቸው በወላይታ ዞን አራት፣ በሀድያ ዞን ሦስት፣ በካፋ ዞን ሁለት፣ በስልጤ ዞን ሁለት፣በ ጉራጌ ዞን ሶስት ወረዳዎች እንዲዋቀሩ ተደርጓል። እንዲሁም በደቡብ ኦሞ ዞን ሁለት፣ በዳውሮ ዞን አምስት፣ በሲዳማ ዞን 11ና በጌዴኦ ዞን ሁለት አዲስ ወረዳዎችን ተዋቅረዋል፡፡ ምክር ቤቱ ያጸደቃቸው አዲስ የአስተዳደር መዋቅሮች
  1. የሀላባ ዞን አስተዳደር በስሩ ያሉ ወረዳዎች
  2. ዌራ ዙሪያ
  3. ድጆ ዌራ
  4. ድጆ
  5. ቁልቶ ከተማ አስተዳደር
  6. የጎፋ ዞን አስተዳደር በስሩ ያሉ ወረዳዎች
  7. ደምባ ጎፋ
  8. ገዜ ጎፋ ወረዳ
  9. ዛላ ወረዳ
  10. ኡባ ደብረ ጸሀይ
  11. ኦይዳ
  12. ሳውላ ከተማ
  13. መሎኮዛ
  14. ጋዳ
  15. ቡልቂ ከተማ
  16. የኮንሶ ዞን አስተዳደር በስሩ ያሉ ወረዳዎች
  17. ካራት ዙሪያ
  18. ከና
  19. ሰገን ዙሪያ
  20. ካራት ከተማ አስተዳደር
የጋሞጎፋ ዞን የነበረው ጎፋ ራሱን ችሎ ሲወጣ ጋሞ ዞን በሚል በስሩ
  1. አርባምንጭ ዙሪያ
  2. ዲታ
  3. ካምባ
  4. ምዕራብ አባያ
  5. ጨንቻ
  6. ደራማሎ
  7. ቁጫ
  8. ቦንኬ
  9. ቦረዳ
10.አርባምንጭ ከተማ 11.ምዕራብ ቁጫ 12.ሰሜን ቦንኬ 13.ጋርዳ ማርታ ወረዳን ይዞ በጋሞ ዞን ስያሜ እንዲቆይ ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ ነባር ዞን አስተዳደሮች ተጨማሪ አዲስ የወረዳ አስተዳደር እርከን የተሰጣቸው ወላይታ ዞን አስተዳደር
  1. ሆቢቻ አባያ
  2. ካዎ ኮይሻ
  3. የበቅሎ ሰኞ
  4. አበላ አባያ
የሀድያ ዞን አስተዳደር
  1. አመካ /የጌጃ ማዕከልን የያዘ/
  2. ሲራሮ ባድዋቾ /ሀንቻ ማዕከልን የያዘ/
  3. ምዕራብ ሶሮ /ጃቾ ማዕከልን የያዘ/
የካፋ ዞን አስተዳደር
  1. ሺሾ እንዴ
  2. ጎባ
የስልጤ ዞን አስተዳደር
  1. ምስራቅ ስልጤ
  2. ሚቶ ዙሪያ
የጉራጌ ዞን አስተዳደር
  1. ሚቄ ከተማ ማዕከል ያደረገ ወረዳ
  2. ኢንሴኖ ማዕከል ያደረገ ወረዳ
  3. ኬላ ማዕከል ያደረገ ወረዳ
በደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር የተፈጠሩት ወረዳዎች
  1. ቢዮ ወባ
  2. ባኮ ዳውላ
በዳውሮ ዞን አስተዳደር የሚቋቋሙት ወረዳዎች
  1. ዝሳ
  2. ታርጫ ዙሪያ
  3. ማሪ ማንሳ
  4. ጌና
  5. ካጪ
በሲዳማ ዞን አስተዳደር
  1. ደራራ ማዘጋጃን ማዕከል ያደረገ ወረዳ
  2. በሌላን ማዕከል ያደረገ ወረዳ
  3. ሀዌላ ጨፌን ማዕከል ያደረገ ወረዳ
  4. ግርጃ ሆኮን ማዕከል ያደረገ ወረዳ
  5. ዳኤላ/ጎንጀቤ/ን ማዕከል ያደረገ ወረዳ
  6. ጫቤን ማዕከል ያደረገ ወረዳ
  7. ተፈሪ ኬላን ማዕከል ያደረገ ወረዳ
  8. ሻፋሞን ማዕከል ያደረገ ወረዳ
  9. ጠጢቻን ማዕከል ያደረገ ወረዳ
10.ቡራን ማዕከል ያደረገ ወረዳ 11.ጭሮነን ማዕከል ያደረገ ወረዳ ጌዴኦ ዞን አስተዳደር
  1. ረጲን ማዕከል ያደረገ ወረዳ
  2. ጨርሶን ማዕከል ያደረገ ወረዳ
በሰገን ህዘቦች ዞን አስተዳደር የሚገኙ የአማሮ፣ የቡርጂ፣ የደራሼና ኸሌ ወረዳ አደረጃጀት፣ በቤንች ማጂ ዞን አዲስ የዞንና የወረዳ አደረጃጀትና በቀድሞው ጋሞጎፋ ዞን የቀረበው የኤዞ ወረዳነትና በከምባታ ጠምባሮ ዞን የአዲሎ ወረዳ ጥያቄ ከህዝብ ጋር ውይይት በማድረግ ምክር ቤቱ በሚሰጠው ውክልና መሰረት እንደሚወሰን ገልጿል፡፡          
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም