ሃና ማሪያም አካባቢ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ መንገድ ተዘግቷል

2015

አዲስ አበባ ጥቅምት 23/2011 በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ሃና ማሪያም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ትናንት በተከሰተ የትራፊክ አደጋ መንገድ መዘጋቱ ተገለጸ።

ትናንት ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት አንድ አይሱዙ መኪና ከሁለት ቱርቦ መኪኖች ጋር ተጋጭቶ እስካሁን ባለመነሳቱ መንገዱ መዘጋቱን በስፍራው ለመንቀሳቀስ የተቸገሩ አሽከርካሪዎች ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል።

መንገዱ ከባድ መኪኖች የሚያልፉበት በመሆኑ በአደጋው ምክንያት ከትላንት ጀምሮ ማለፍ አለመቻላቸውን አሽከርካሪዎች ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

በመሆኑም የሚመለከተው አካል መንገዱን እንዲያስከፍት ጠይቀዋል።