ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሆላንድ ክለብ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋል

143
አዲስ አበባ ግንቦት 14/2010 የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ከሆላንዱ ቪቪቪ ቬኔሎ ክለብ ጋር ሐምሌ 6 ቀን 2010 ዓ.ም የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋል። ክለቡ ከወዳጅነት ጨዋታ በተጨማሪ የልምድ ልውውጥ እንደሚያደርግ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር አስታውቋል። ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐምሌ 6 ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከቪቪቪ ቬኔሎ ክለብ ጋር በሆላንድ ዲኮዬል በሚገኘው ሲያኮን ስታዲየም የወዳጅነት ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል። ክለቡ የወዳጅነት ጨዋታውንና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ሐምሌ 4 ቀን 2010 ዓ.ም ወደ ስፍራው እንደሚያቀና ተገልጿል። የክለቡ ተጨዋቾች በሆላንድ በሚኖራቸው ቆይታ በአገሪቱ የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ የመዝናኛ ስፍራዎችንና ተቋማትን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም