የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና መመስረት በአህጉሪቱ የምጣኔ ኃብታዊ ትስስርን ለማጠናከርና ሰፊ የገበያ እድሎችን ለመፍጠር ያስችላል

69
አዲስ አበባ ጥቅምት 13/2011 የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና መመስረት በአህጉሪቱ አባል አገራት መካከል የምጣኔ ኃብታዊ ትስስርን ለማጠናከርና ሰፊ የገበያ እድሎችን ለመፍጠር እንደሚያስችል ባለሙያዎች ተናገሩ። የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና የተጠነሰሰው ከዛሬ ስድስት ዓመት በፊት በአዲሰ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት መሪዎች 18ኛው መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው። ቀጠናው  ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን የሚልቀውን የአፍሪካ ህዝብና ከ 3 ነጥበ 4 ትሪሊዮን ዶላር በላይ የሆነውን አጠቃላይ ብሄራዊ ገቢ ያቀናጀ ግዙፍ የገበያ እድል የመፍጠር ዓላማ አለው። ይህም አፍሪካን በዓለም ላይ ከፍተኛ ምጣኔ ኃብት ከገነቡ ዓለማት ተርታ እንድትሰለፍና ጠንካራ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችላት መሆኑን ነው ኢዜአ ያነጋገራቸው የምጣኔ ኃብት ባለሙያዎች የተናገሩት። በቀጠናው ያሉ ዜጎች በሌሎች የአፍሪካ አገራት ነጻ የንግድና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ማድረግ የሚያስችል እና እድል የሚፈጥር መሆኑም ይጠቀሳሉ። በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ አገሮች መካከል ያለው የንግድና ገበያ ልውውጥ ዝቅተኛ መሆኑን የሚናገሩት ሙያተኞቹ የቀጠናው መመስረት በአፍሪካ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደረግ ጠንካራ ገበያ ለመፍጠር ያስችላል ይላሉ። ጉዳዩን የሚያስረዱት የምጣኔ ሃብት ባለሙያና ኢንቬስተርአቶ ዘመዴነህ ንጋቱ አፍሪካ በጣም ትልቅ ኮንቲኔንት ናት ከዌስት፣ ኢስት ሳውዝ ኖርዝ ያለው አንዳንድ አካባቢዎች የራሳቸውን የፍሪ ትሬድ ኤሪያ ፈጥረዋል ፡፡ የአፍሪካ አገሮች በመካከላቸው ያለው የንግድ ልውውጥ በጣም አናሳ ነው እስከዛሬ ድረስ በጣም ብዙ የአፍሪካ አገሮች የሚነግዱት ከአውሮፓ ወይም ከኤዥያ ጋር ነው አብዛኞቹ ንግዳቸው የተቆራኘው ከተለያዩ አለማት ጋር ነው አፍሪካ ውስጥ እርስ በእርስ ያለው የንግድ ልውውጥ በጣም ዝቅተኛ ነው ይሄ መለወጥ መቻል ያለበት ነው።”ዶክተር አሰፋ አድማሴ የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ናቸው፡፡  በመሆኑም በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ቢጠናከር ኢትዮጵያን ጨምሮ በቀጠናው ያሉ አምራቾች ምርቶቻቸውን በተለያዩ አገሮች ተዘዋውረው ለመሸጥና ለማስተዋወቅ ትልቅ እድል የሚፈጥር መሆኑንም ይገልጻሉ።አፍሪካውያን እርስ በርስ ንገድ ማድረግ ኢኮኖሚ ጠቀሜታ  ጉልህ እንደሆነ የሚያስረዱት አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ የምጣኔ ሃብት ባለሙያና ኢንቬስተር ናቸው፡፤ አፍሪካ ውስጥ  አምራቾች ሊጠቀሙ የሚችሉበት  ሰፊ  የገበያ እድል  አለ  እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግርና ልውውጥ በመኖሩ ይህን ማጠናከር አስፈላጊነቱን የሚያስረዱትዶክተር አሰፋ አድማሴ የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ናቸው፡፡   ለንግድ ቀጠናው ተግባራዊነትም በተለይ የግሉ ዘርፍ ንቁ ተሳትፎና ድጋፍ ወሳኝ ሚና ሊታከልበት እንደሚገባም ገልጸዋል።  የአፍሪካ አገሮች አህጉር አቀፍ ነፃ የንግድ ቀጠና መመስረት የሚያስችላቸውን ስምምነት ባለፈው 2010 ዓም በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው 10ኛው የአፍሪካ ህብረት ልዩ ጉባኤ ላይ መፈረማቸው ይታወሳል። ከ15 እስከ 22 የሚሆኑት አባል አገራት ስምምነቱን በአገራቸው ህግ አውጪ አካል ወይም ፓርላማ ከጸደቀ በኋላ ተግባራዊ እንደሚሆን ይጠበቃል። የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት እ.ኤ.አ በ2020 የአፍሪካን አገራት የንግድ ልውውጥ በ52 በመቶ እንደሚጨምረው የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን መረጃ ያመለክታል።            
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም