አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ አገሩ ተመለሰ

100
አዲስ አበባ ጥቅምት 11/2011 አትሌቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ቤተሰቦቹ፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት፣ታዋቂ አትሌቶች እና ወዳጆቹ አቀባበል አድርገውለታል። በአትሌቱ አቀባበል የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፣ አዲሱ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ፣ የኢትዮጵያ  ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ  እና ሌሎች ኃላፊዎች ተገኝተዋል። አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2016 በብራዚል በተካሄደው የሪዮ ኦሊምፒክ ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ በማራቶን ተሳትፎ የብር ሜዳሊያ ያስገኘ ሲሆን፤ በውድድሩ መጠናቀቂያ አካባቢ ሲደርስ በወቅቱ በአገሪቷ የነበረውን ሁኔታና በመንግስት ላይ ያለውን ተቋውሞ በመግለጽ ይታወቃል። በዚህ ምክንያትም ላለፉት ሁለት ዓመታት ኑሮውን ከኢትዮጵያ ውጭ በአሜሪካን አድርጎ ቆይታል። አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በተወዳደረባቸው የማራቶንና ግማሽ ማራቶን ውድድሮች አምስት የወርቅ፣ ሁለት የብርና ሁለት የነሐስ ሜዳሊያ  ያገኘ አትሌት ነው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም