ኢትዮጵያ ቡና የአዲስ አበባ ዋንጫ አሸናፊ ሆነ

60
አዲስ አበባ ጥቅምት 10/ 2011 ኢትዮጵያ ቡና ባህር ዳር ከተማን 4ለ1 በማሸነፍ  የአዲስ አበባ ዋንጫ አሸናፊ ሆነ፡፡ ዛሬ በአዲስ አበባ በተካሄደው 13ኛው የአዲስ አበባ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ የተገናኙት ኢትዮጵያ ቡና ና ባህር ዳር ከተማ ነበሩ፡፡ የፍጻሜ ጨዋታውን ኢትዮጵያ ቡና ከእረፍት በፊት  ባስቆጠሩት  ሶስት ጎሎችና ከእረፍት መልስ ባስቆጠሩት አንድ ጎል  ታግዘው 4 ለ 1 በሆነ ውጤት የፍጻሜ ጨዋታውን በበላይነት አጠናቋል፡፡ ለኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት ከሉሽያ አልአሰንና በጨዋታ  አምበሉ ሳምሶን ጥላሁን ብፍጹም ቅጣት ምት   አውወከር ናስሩ  ደግሞ  አንድ በፍጹም ቅጣት  አንድ በጨዋታ   ጎሉቹን አስቆጥረዋል  ፡፡ ለባህር ዳር ከተማ ከሽንፈት ያልዳኑበትን  ጎል ተቀይሮ የገባው እንዳለ ደባልቄ  ከእረፍት መልስ አስቆጥሯል፡፤ የፍጻሜ ጨዋታውን ኢንተርናሸናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ የመሩት ሲሆን በርካታ የሁለቱ ቡድን ደጋፌዎች ጨዋታውን ተከታትለውታል፡፡  ለጨዋታውም  ከፍተኛ ድምቀት ሰጥተውታል የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ ታከለ ሁማ ና የበአር ዳር ከንቲባ አቶ  ሙሉቀን አየው በክብር እንግድነት በመገኘት  ጨዋታውን ተከታትለዋል፡፡ በጨዋታው ኢንተርናስናል ዳኛ በአምላክ የፍጹም ቅጣት ምት ለተቃወሙ አራት  የባህር ዳር ተጨዋቾች ቢጫ ካርድ አይተዋል፡፡ አሰልጣኝ ፓውሎስ ጌታቸው ከእረፍት  መልስ በኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ ከሜዳ እንዲወጣም  ተደርጓል፡፡ በሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና የተሻለ እንቅስቃሴና የጎል ሙከራዎችን ማድረግ ችሏል፡፡ ኢትዮጵያ ቡናና ባህር ዳር ከተማ በእንደዚህ አይነት ትልቅ ጨዋታ ሲገናኙ ለመጀመሪያ ግዜ ነው፡፡ ባህር ዳር ከተማ በብሄራዊ ሊግ ከምድቡ በአንደኝነት በማጠናቀቅ ወደ ፕሪምየር ሊጉ በዚህ አመት መሸጋገሩ ይታወቃል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም