የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ጉባዔ ተጀመረ

59
መቀሌ ጥቅምት 10/2011 የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ ምክር ቤት አምስተኛ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባዔው ዛሬ ተጀመረ። ለሦስት ቀናት በሚካሄደው ጉባዔ በካቢኔውና  በምክር ቤቱ  የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ  ላይ ይወያያል። እንዲሁም የቀበሌ ገበሬ ማህበራት የመሬት ዳኝነት ስልጣንና ተግባር ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት ማስተላለፊያ ዓዋጆችን ያፀድቃል። በተጨማሪም የካቢኔውን ሹመት ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል። የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ቅድሳን ነጋ ምክር ቤቱ የሚያወያይባቸውን  አጃንዳዎች አቅርበው  ፀድቀዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም