በደቡብ ክልል ግምቱ ከአምስት ሚሊዮን ብር የሚበልጥ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ

70
ሐዋሳ ጥቅምት 9/2011 በደቡብ ክልል ግምቱ ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ዕቃ በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ መያዙን በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሃዋሳ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ በጽህፈት ቤቱ የደንበኞች አገልግሎት የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ዓለማየሁ ከበደ ለኢዜአ እንደገለጹት ከኅብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ በመነሳት የፌዴራል ፖሊስ አባላት ባደረጉት ክትትል ዕቃው ተይዟል። ከኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል አዳዲስና አሮጌ አልባሳት፣ ሶላር መብራቶችና የኮስሞቲክ ዕቃዎች ይገኙበታል፡፡ ዕቃዎቹ  የተያዙት ከዓርባምንጭ ወደ ወላይታ በመጓዝ ላይ በነበረ የጭነት መኪና ውስጥ  ነው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም