የባህር ዳር ከተማ ለአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ፍጻሜ አልፏል

61
አዲስ አበባ ጥቅምት 7/2011 በ13ኛው የአዲስ  አበባ ከተማ ዋንጫ የባህር ዳር ከተማ ለፍጻሜ ያለፈ የመጀመሪያው ክለብ ሆኗል። በአዲስ አበባ ስታዲየም ዛሬ በተካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የመጀመሪያ ግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ባህር ዳር ከተማ መከላከያን 3ለ2 በማሸነፍ ለፍጻሜ ማለፉን አረጋግጧል። ለባህርዳር ከተማ ፍቅረ ሚካኤል ዓለሙ፣ ግርማ ዲሳሳና ፍቃዱ ወርቁ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ለመከላከያ ደግሞ አዲሱ ተስፋዬና አቅሌሲያስ ግርማ ናቸው ግቦቹን ያስቆጠሩት። በዚሁ መሰረት ባህርዳር ከተማ የፊታችን ቅዳሜ በሚደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ከጅማ አባ ጅፋርና ከኢትዮጵያ ቡና አሸናፊ ጋር የሚጫወት ይሆናል። የባህር ዳር ከተማው ግርማ ዲሳሳ የጫወታው ኮከብ ሆኖ በመመረጡ ከድሬደዋ ከተማው አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ እጅ የተዘጋጀለትን ሽልማት ተቀብሏል። ሁለተኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ እየተከናወነ ነው።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም