ቮልስ ዋገን ኩባንያ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት አለው - ኢዜአ አማርኛ
ቮልስ ዋገን ኩባንያ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት አለው
77
ጥቅምት 7/2011 ቮልስ ዋገን ኩባንያ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገለፀ የጀርመን የመኪናዎች አምራች ድርጅት ቮልስ ዋገን ኩባንያ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል፡፡ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የቮልስ ዋገን ኩባንያ አመራሮችን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ በውይይታቸውም ኩባንያው በኢትዮጵያ ፋብሪካ ለማቋቋም በጥናት ላይ እንደሚገኝ ገልጾ ለአውቶ ኢንዱስትሪ አመቺ ሁኔታ ከተፈጠረ ኢንቨስት ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ መንግስት ለመኪና ማምረቻ ኢንዱስትሪ ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደረግ ገልጸው ኩባንያው በተቻለ ፍጥነት ጥናቱን አጠናቆ የኢንቨስትመንት ውሳኔውን እንዲያሳውቅ መጠየቃቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡