አምስት አስፈጻሚ አካላት ተጠሪነታቸው ለምክር ቤቱ እንዲሆን ተወሰነ

59
አዲስ አበባ ጥቅምት 6/2011 የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ኤጀንሲን ጨምሮ አምስት ተቋማት ተጠሪነታቸው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሆን ተወሰነ። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 2ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ኤጀንሲ፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እንዲሁም የፌዴራል የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ተጠሪነታቸው ቀጥታ ለፓርላማው እንዲሆን ወስኗል። በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ፣ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣ የአካባቢ፣ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን፣ የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ፣ ቱሪዝም ኢትዮጵያና የቤተ መንግስት አስተዳደር ተጠሪነታቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲሆን ተወስኗል። ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎው የመንግስት አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር የሚወስነውን አዋጅ ቁጥር 1097/2011 በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም