የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ20 አዳዲስ የካቢኔ ሹመት ውስጥ 50 በመቶ ሴቶች ሆነው እንዲያገለግሉ አፀደቀ - ኢዜአ አማርኛ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ20 አዳዲስ የካቢኔ ሹመት ውስጥ 50 በመቶ ሴቶች ሆነው እንዲያገለግሉ አፀደቀ
122
አዲስ አበባ ጥቅምት 6/2011 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ20 አዳዲስ የካቢኔ ሹመት ውስጥ 50 በመቶ ሴቶች ሆነው እንዲያገለግሉ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበውን ሹመት አፀደቀ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባውን እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሚሾሙት 20 ካቢኔዎች ውስጥ 10 ሴቶች ሆነው በተሰጣቸው ሃላፊነት እንዲያገለግሉ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል። የካቢኔ ሹመቱ የቀረበው የአስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል የቀረበውን አዲስ ረቂቅ አዋጅ በምክር ቤቱ መፅደቁን ተከትሎ ነው። በዚህም መሰረት የሹመቱ ዋና መስፈርት ብቃት፣ የትምህርት ዝግጅትና ለውጥን የመምራት አቅም መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከሚሾሙት ካቢኔዎች 50 በመቶ ወይም ከ20 ዎቹ 10 ሴት ካቢኔዎች መሆናቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል። ይህም በኢትዮጵያ ምንአልባትም በአፍሪካ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑም በምክር ቤቱ ተገልጿል። ከነዚህም ውስጥ፦
- የሰላም ሚኒስቴር---------------- ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል
- የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር----------ኢንጂነር አይሻ መሐመድ
- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር----------ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ
- የገንዘብ ሚኒስቴር- አቶ አህመድ ሺዴ
- የግብርና ሚኒስቴር --------------------አቶ ኡመር ሁሴን
- የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር---ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር
- የገቢዎች ሚኒስቴር---ወይዘሮ አዳነች አቤቤ
- የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር - ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ
- የትራንስፖርት ሚኒስቴር----ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ
- የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ----አቶ ጃንጥራር አባይ
- የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር--------ዶክተር ሳሙኤል ሁርጶ
- የትምህርት ሚኒስቴር----ዶክተር ጥላዬ ጌቴ
- የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር----ዶክተር ሂሩት ወልደማሪያም
- የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር --- ወ/ት የአለምፀጋይ አስፋው
- ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ---ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ
- የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ----ዶክተር ሂሩት ካሳው
- የፌደራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር ሚኒስቴር - በሰላም ሚኒስቴር ስር የተጠቃለለ
- የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት - በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሰክሬታሪያት የሚተካ
- የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር - የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር የተጠቃለሉ
- የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር- በአንድ ላይ የተዋሃዱ
- የከተማ እና ቤቶች ልማት ሚኒስቴር - ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ጋር የተዋሃዱ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ መፅደቁንና በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተግባር እንደሚገባም በምክር ቤቱ ውይይት ላይ ተገልጿል።