ቤተክርስቲያኗ የኢትዮጵያና የሩስያን ግንኙት ለማጠናከር እንደምትሰራ ገለፀች

81
አዲስ አበባ ግንቦት 13/2010 በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትሰራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገለፀች። ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵ›,ወውውተሰ   ከጀሀገፈረቀቀወረተቴያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ኃይማኖት በራሽያ ሞስኮ ለስድስት ቀናት ጉብኝት አድርገው ተመልሰዋል። ፓትርያርኩ በጉብኝታቸው የመላው ሩስያ ቅዱስ ፓትርያርክ ክሪል፤ ለቅዱስነታቸው በሞስኮ መድኀኔዓለም ካቴድራል 'የእንኳን ደህና መጡ' ንግግር አድርገዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታላቅ ቤተክርስቲያን ስትሆን  በአባቶችና በእናቶች ጥንካሬ ተጠብቃ ለዓለም አርአያ ሆና የምትጠቀስ መሆኗን ገልፀዋል። በቅዱስነታቸው የተመራው የልኡካን ቡድን ወደ ሩስያ ማቅናቱ ቀድሞ ለነበረው ጠንካራ ግንኙነት ጉልበት እንደሚሆንም ነው ቅዱስ ክሪል የተናገሩት። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ  በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ በሁለቱ አብያተክርስቲያናት መካከል የነበረው የሁለትዮሽ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የተለያዩ ስልጠናዎች እንዲመቻቹ ጠይቀዋል። ፓትርያርኩ በጉብኝታቸው ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን የሁለቱን አብያተ ክርስቲያናት የቆየ ግንኙነት  ከ120 ዓመታት በላይ ማስቆጠሩን ተናግረዋል። ከአሁን በፊት በራሽያ የተማሩ የቤተ ክርስቲያን አባቶች በከፍተኛ የቤተ ክርስቲያኒቱ የስልጣን እርከን በማገልገል ላይ መሆናቸውን አስታውሰው አሁንም ተግባሩ እንዲቀጥል ምኞታቸውን ገልጸዋል። በመካከሉ ግን እየተቀዛቀዘ የመጣውን የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ዳግም ለማጠናከር ቤተክርስቲያኗ እየሰራች መሆኑንም ጠቁመዋል። የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርቲያን ጥንታዊና ታሪካዊ መሆኗንና ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የረጅም ጊዜ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደነበራቸው ተናግረዋል። ግንኙነቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ልዩ ልዩ ስልጠናዎች እንደሚዘጋጁም አብራርተዋል። በማህበራዊ ዘርፍ ልማት በጋራ ለመስራትና የተቋረጠው የትምህርት ዕድል መቀጠል በሚችልበት ሁኔታ ላይም መክረዋል። የሩስያ ምክትል አፈ ጉባኤ ሚስተር ኒኮላይ ፌዮዶሮብ ከቅዱስነታቸው ጋር በተወያዩበት ወቅት የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ግንኙነት ለአገራዊ ግንኙነቱ ጠቃሚ እንደሆነ ገልጸዋል። አፈ ጉባዔው 'ታሪካዊው የቅዱስነታቸው ጉብኝት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር መልካም አጋጣሚ ነው' ማለታቸውን የቤተክርስቲያኗ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ለኢዜአ በላከው መግለጫው አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም