ዋልያዎች በኬንያ አቻቸው 3ለ0 ተሸነፉ

78
አዲስ አበባ ጥቅምት 4/2011 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን /ዋልያዎቹ/ በ2019 በካሜሮን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በኬንያ አቻቸው ሶስት ለባዶ ተሸነፉ። ዛሬ በኬንያ ካንሳራኒ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በመጀመሪያው ግማሽ ሁለት ጎል አስተናግደው እረፍት የወጡ ሲሆን ከእረፍት መልስ በቅጣት ምት በገባባቸው ሶስተኛ ጎል ባጠቃላይ ሶስት ለባዶ ተሸንፈዋል። ዋልያዎቹ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያው ካዛሬው ጨዋታ በፊት ባደረጉት ጨዋታዎች በጋና በሰፊ ጎል ተሸንፈዋል፤ ሴራሊዮንን ሲያሸንፉ በሜዳቸው ከኬንያ አቻቸው ጋር የለምንም ግብ ተለይተዋል። በዚህ የማጣሪያ ውድድር እያንዳንዱ ሀገር ስድስት ጨዋታ የሚያከናውን ሲሆን ዋልያዎቹ አምስተኛ ማጣሪያ ጨዋታቸውን በህዳር ወር በሜዳቸውና በደጋፊያቸው ፊት ከጋና ጋር  ይጫወታሉ። ቀሪውን የመጨረሻ ማጣሪያ ጨዋታ ደግሞ ለጊዜው በፊፋ ከዓለም አቀፍ ውድድር እገዳ ከተነሰላት ከሴራሊዮን ጋር በመጋቢት ወር 2011 ዓ.ም ያካሄዳሉ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም