ድርጅቱ ለተፈናቃዮች 3 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ድጋፍ አደረገ

51
ነቀምቴ ጥቅምት 4/2011 የአዲስ አበባ ወጣቶች በጎ አድራጎት ድርጅት በቤኒሻንጉል ጉሙዝና ኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን አዋሳኝ ወረዳዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ግምቱ 3ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የሆነ ዕርዳታ አደረገ ፡፡ የድርጅቱ ተወካይ ወጣት ኑረዲን ነስሮ ድጋፉን ለምሥራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደር ጽህፈት ቤት ሲያስረክብ እንደተናገረው ድርጅቱ በአካባቢዎቹ በተፈጠረው ግጭት የተፈናቀሉትን ወገኖች ችግር ለማቃለል ድጋፉን አድርጓል። ድርጅቱ ለተፈናቃዮቹ ከለገሳቸው መካከል አልሚ ምግብ፣ የሕፃናት ወተት፣ ብርድ ልብሶች፣ የአዋቂና የሕፃናት አልባሳትና ጫማዎች ይገኙበታል። የምሥራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ማሙሻ ኃይሉ ዕርዳታውን ድርጅቱ ላደረገው ድጋፍ  አመስግነው፣ ወጣቶቹ ያደረጉት አስተዋጽኦ ለሌሎች ጥሩ ምሳሌ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩልም የቡኖ በደሌ ከተማ አስተዳደርና በአዲስ አበባ የሚኖሩ የጊዳ አያናና የሐሮ ሊሙ ተወላጆች ለተፈናቃዮቹ 750ሺህ ብር የሚገመት ድጋፍ አድርገዋል፡፡ የበደሌ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ደበላ ያደታ ግምቱ 350ሺህ ብር የሆነ 50ኩንታል ዱቄት፣ 50 ኩንታል መኮሮኒ፣100 ካርቶን ብስኩትና 300 ብርድ ልብሶችንነና በተጨማሪም 50ሺህ ብር ገንዘብ ለአስተዳደሩ አስረክበዋል ገቢ መደረጉን አስታውቀዋል። እንዲሁም የጊዳ አያናና የሐሮ ሊሙ ተወላጆች ግምቱ 400 ሺህ የሚሆን100 ፍራሾችና 720 ብርድ ልብሶችን በተወካያቸው አማካይነት ዕርዳታውን አስረክቧል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም