የኢትዮ - ኤርትራ የሰላምና የፍቅር ሩጫ ጥቅምት 18 ይካሄዳል

79
አዲስ አበባ ጥቅምት 2/2011 የኢትዮ - ኤርትራ የሰላምና የፍቅር የሩጫ ውድድር ጥቅምት 18 ቀን 2011 ዓ ም በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚካሄድ ተገለጸ። መነሻና መድረሻውን በአዲስ አበባ  መስቀል አደባባይ ያደረገው ይህ የሩጫ ውድድር የ10 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን ነው። ውድድሩን ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በክብር እንግድነት በመገኘት ሩጫውን ያስጀምራል ተብሏል። የውድድሩ ዋና አስተባባሪ አቶ ሰለሞን ታፈረ እንደገለጹት፤ የሩጫ ውድድሩ ዓላማ የኢትዮጵያንና የኤርትራን ግንኙት በማሳደግ የሰላምና  የአንድነት ግንኙነታቸውን ማጠናከር ነው። ጂኤምኤስ የተባለው የማስታወቂያ ድርጅት አዘጋጅነት በሚካሄደው በዚህ ውድድር ከ20 ሺህ በላይ ሰዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል። በውድድሩ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ኤርትራውያን ከሚያደርጉት ተሳትፎ ባሻገር ከኤርትራ መጥተው ለመሳተፍ ከ200 በላይ የሆኑ ሰዎች እንደተመዘገቡ አቶ ሰለሞን ጠቁመዋል። የኢትዮ ኤርትራ የሰላም የፍቅር፣ የአንድነት የጎዳና ላይ ሩጫ ለመሳተፍ  እስካሁን 15 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች መመዝገባቸው ታውቋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም