የጣሊያንና ኢትዮጵያ የ696 ሚሊዮን ብር የድጋፍና የብድር ስምምነት ተፈራረሙ

2101

አዲስ አበባ ጥቅምት 1/2011 ጣሊያን በኢትዮጵያ የከተሞች የውሃና ፍሳሽ አገልግሎትን ለማሻሻል የሚውል የ696 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገች።

የድጋፍ ሥምምነቱን የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አድማሱ ነበበና በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አርቱሮ ሉዚ ፈርመውታል።

በሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሃጂ ኢብሳ እንደተናገሩት፤ ስምምነቱ በአራት መካከለኛና ዝቅተኛ ደረጃ የከተሞች የውሃና ፍሳሽ አገልግሎትን ለማሻሻል ይውላል።

ከድጋፉ 158 ሚሊዮን ብሩ በድጋፍ መልክ ቀሪው 538 ሚሊዮን ብር ደግሞ በረዥም ጊዜ የሚከፈል ብድር መሆኑን ጠቁመዋል።

ሥምምነቱ በጣሊያን የልማት ትብብርና በውኃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር በጋራ ተግባራዊ እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

ይህም የከተሞችን የውኃና ፍሳሽ አገልግሎት በማሻሻል የነዋሪዎችን ጤና ለመጠበቅ ያለመ መሆኑን አቶ ሃጂ ተናግረዋል።