የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

1556

አዲስ አበባ ጥቅምት 1/2011 የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ለይፋዊ የስራዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ለሁለት ቀናት በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሏል።

የሁለቱ አገሮች መሪዎች በኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካና ማህበራዊ ጉዳዮች እንዲሁም በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎም ይጠበቃል።