ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በጋምቤላ ክልል የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ይጎበኛሉ

77
ግንቦት 12/2010 የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት በጋምቤላ ክልል የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ይጎበኛሉ፡፡ ጉብኝቱ ከሚያተኩርባቸው ስራዎች መካከልም የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ፣ ጋምቤላ ሆስፒታል፣ የመብራት ሀይል ማከፋፈያ ጣቢያ፣ የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት፣ የክልሉ መስተዳድር ምክርቤትና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጉብኝቱ አስቀድመው በጋምቤላ ስታዲየም ተግኝተው ለክልሉ ህዝብ ንግግር ያደርጋሉ፡፡ ዶክተር ዐቢይ ትናንት ማምሻውን በኅዳር 29 የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተወያይተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም