በተባበሩት መንግስታት የአሜሪካ አምባሳደር ኒኪ ሃሌይ ሃላፊነታቸውን ለቀቁ

2423

መስከረም 30/2011 የአሜሪካ ቋሚ መልዕክተኛ ኒኪ ሃሌይ ሃላፊነታቸውን በራሳቸው ፈቃድ መልቀቃቸውን በበሲ ዘግቧል፡፡

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቢሯቸው ኒኪ ሃሌይን አግኝተው ያናገሯት ሲሆን ትልቅ ስራ ነው የሰራችው ሲሉም ተናግረዋል።

በኒኪ የሃላፊነት ቦታም አዲስ ሰው ከሁለት እስከ ሶስት ሳምንት ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሾሙ ጠቁመዋል።

በተባበሩት መንግስታት የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው ሊሾሙ ይችላሉ ተብለው ከፍተኛ ግምት የተሰጣቸው የትራምፕ የቀድሞ  የፀጥታው ምክር ቤት ምክትል አማካሪ ዲና ፖዌል  ናቸው።

ልጃቸው ኢቫንካ ትራምፕ ሊሾሙ ይችላሉ የሚሉ ግምቶች ቢኖሩም ዶናልድ ትራምፕ በቤተሰባዊ ዝምድና ሹመት በመስጠት እንደሚያስከስሳቸው መናገራቸው የኢቫንካን የአምባሳደርነት ሹመት እድል ዝቅተኛ አድርጎታል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት ያህል በተባበሩት መንግስታት የአሜሪካ ቋሚ መልዕክተኛ የነበሩት ኒኪ ሃሌይ ሃላፊነታቸውን ለመልቀቅ ያስገደዳቸውን ምክንያት በግልፅ አልተናገሩም።