ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ቱርክ ሄዱ

91
አዲስ አበባ መስከረም 29/2011 ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ወደ ቱርክ አቅንተዋል። ፕሬዝዳንቱ ወደ ቱርክ ያመሩት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ኤርዶጋን ባቀረቡላቸው ግብዣ መሰረት ሲሆን በቱርክ-አፍሪካ የቢዝነስ መድረክ ላይ እንደሚገኙም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኢዜአ ገልጿል። ፕሬዚዳንቱ ከቱርክ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ከትልልቅ ኩባንያዎች ኃላፊዎች ጋር በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በሌሎች የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩም ይጠበቃል። መድረኩ የቱርክ ባለሀብቶች በአፍሪካ ያላቸውን ኢንቨስትመንት እንዲያሰፉና እንዲያጠናክሩ እድል ይፈጥራል ተብሏል። በመድረኩ ላይ የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ፓል ካጋሜ እና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ መሀመት እንደሚገኙም ይጠበቃል። በኢትዮጵያ በበርካታ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ከተሰማሩ ቀዳሚ አገራት መካከል ቱርክ ተጠቃሽ ናት።        
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም