ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ የተጠቀሙ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና ድርጅቶች ተሸለሙ

211
ባህር ዳር መስከረም 27/2011 ባለፈው ዓመት ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባርና ለሚዛናዊ መረጃ የተጠቀሙ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና ድርጅቶች ትናንት ተሸለሙ። በ16 የውድድር ዘርፎች እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል። “ማህበራዊ ሚዲያ ለበጎ ተግባርና ማህበራዊ ኃላፊነት በሚል” መሪ ሃሳብ ለሁለተኛ ጊዜ በተዘጋጀው የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሂሩት ካሳውንን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ በውድድሩ 49 ሺህ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የተጠቆሙ ሲሆን፣ ከነዚህም 100 ዎቹ በመጨረሻ ዕጩነት ቀርበውበት ነበር። በባህልና ቱሪዝም ዘርፍ- ጋዜጠኛ ጌትነት ተመስገን፣ በበጎ አድራጎት ዘርፍ-አቡ ጌዳ ሮተርስ ክለብ፣ በስነ-ጥበባዊ ምስሎችና ትርክቶች-እያዩ ገነት፣በንግድና ቢዝነስ ዘርፍ- ሄሎ መርካቶ ተሸልመዋል። እንዲሁም በትምህርትና ማህበረሰብ ዘርፍ- ቡክ ፎር ኦል ድረገጽ እና በፈጣን ወቅታዊ መረጃ ዘርፍ-ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን ከተሸላሚዎቹ መካከል ናቸው፡፡ ታላሚዎቹ ማህበራዊ “ጣና አዋርድ”  የሚል ስያሜ የተሰጠውን ይህን የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብር ሰለሞኒክ ኢንተርቴይመንትና ዘመራ መልቲ ሚዲያ የተባሉ  ድርጅቶች በጋራ ያዘጋጁት ነው፡፡ “ጣና አዋርድ”  የሚል ስያሜ የተሰጠውን ይህን የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብር ሰለሞኒክ ኢንተርቴይመንትና ዘመራ መልቲ ሚዲያ የተባሉ  ድርጅቶች በጋራ ያዘጋጁት ነው፡፡ “ጣና አዋርድ”  የሚል ስያሜ የተሰጠውን ይህን የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብር ሰለሞኒክ ኢንተርቴይመንትና ዘመራ መልቲ ሚዲያ የተባሉ  ድርጅቶች በጋራ ያዘጋጁት ነው፡፡ ማህበራዊ ሚዲያን ለማህበረሰባዊ ኃላፊነትና የአገር አንድነትን ለማጠናከር  የተጠቀሙ ግለሰቦችና ድርጅቶች መሆናቸው ተገልጿል። ተሸላሚ ግለሰቦች በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ዕድል የተሰጣቸው ሲሆን፣ ለአሸናፊ ድርጅቶች ደግሞ  የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ከ''ጣና አዋርድ'' አዘጋጆች  መካከል አንዱ  አቶ ሰለሞን ምህረት በባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደገለጹት ሽልማቱ ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሚለቁትን መረጃ ለአገር እድገትና ለማህበረሰባዊ ለውጥ እንዲያውሉት ለማበረታታት  ታልሞ የተዘጋጀ ነው። አንዳንድ ግለሰቦችና ድርጅቶች ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም አገራዊ አንድነትን ከማጠናከር ይልቅ ልዩነትን፣ መቻቻልን ሳይሆን መቃቃርን የሚያጎሉ መረጃዎችን በመልቀቅ  የህዝቦች አንድነትና አብሮ የመኖር እሴትን በመሸርሸር ላይ እንደሆኑም ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ማህበራዊ ሚዲያን ለአገራዊ አንድነት መጠናከርና ለማህበረሰባዊ ለውጥ  የተጠቀሙ ግለሰቦችና ድርጅቶች መኖራቸውን የተናገሩት አቶ ሰለሞን፣ ሽልማቱ ለእነዚህ አካላት እውቅና በመስጠት ተከታዮች እንዲበዙ ከማድረግ አንጻር የጎላ ሚና አለው  ብለዋል፡፡ በግለሰብ ደረጃ በታሪክ ዘርፍ የ''ጣና አዋርድ'' ተሸላሚው ጋዜጠኛ ኢዮብ እንዳለው የአገሩን ታሪክ ለማወቅና ለማሳወቅ ካለው ጉጉት የተነሳ ታሪክን በማንበብና በማመሳከር እንዲሁም በአካል ወደተለያዩ ሥፍራዎች በመሄድ የሚያገኘውን መረጃ ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ለህዝብ እያደረሰ ነው፡፡ ማህበራዊ ሚዲያን በአግባቡ ከተጠቀሙበት ለህዝቡ ዓይንና ጆሮ መሆን ይቻላል ያለው ጋዜጠኛ ኢዮብ፣ ተጠቃሚዎች አላስፈላጊ ሃሳቦችን ከማሰራጨት ይልቅ፣ አገራዊ አንድነትንና ማህበረሰባዊ ጥቅምን የሚያስገኙ መረጃዎች ላይ መስራት አለባቸው ብሏል። ሽልማቱ የበለጠ ለመሥራት እንዳነሳሳውና ሌሎችም እንዲበረታቱ ያግዛል ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል። በሥነ-ጽሁፍ  ዘርፍ ተሸላሚው መዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እንደገለጸው ታላቅ የነበረች አገር ኢትዮጵያን ዳግም ወደ ገናናነቷ ለመመለስ ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ግለሰቦችና ድርጅቶች በኃላፊነት ሊሰሩ ይገባል። በአብዛኛው ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች  ሚዛናዊ ባልሆነና አገራዊ አንድነትን ከማጠናከር ይልቅ ልዩነትን በመስበክ ኅብረተሰቡን ለጉዳት የሚዳርጉ መረጃዎች ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ ገልጿል፡፡ “ሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችና ኢትዮጵያውያን ይችን ገናና አገር ወደ ነበረ ክብሯ ለመመለስ መረጃን በኃላፊነት መጠቀምና ማጋራት ይጠበቅብናል “ ሲል አሳስቧል። ዘንድሮ ዘርፉን በማስፋት ወደ 16 ያደገው የ''ጣና አዋርድ'' ባለፈው አመት በ11 ዘርፎች  ሽልማት መስጠቱ ይታወሳል፡፡ “ጣና አዋርድ”  የሚል ስያሜ የተሰጠውን ይህን የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብር ሰለሞኒክ ኢንተርቴይመንትና ዘመራ መልቲ ሚዲያ የተባሉ  ድርጅቶች በጋራ ያዘጋጁት ነው፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም