በቡራዩ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል ዝግጅት ተጠናቋል

75
አዲስ አበባ መስከረም 26/2011 ነገ በቡራዩ መልካ አቴቴ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ። የበዓሉን አከባበር አስመልክቶ ዛሬ በቡራዩ በተካሄደ ውይይት አባ ገዳዎች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የኦሮሚያ ወጣቶችና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል። በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ከሚከበረው የኢሬቻ በዓል ቀጥሎ ትልቅ ደረጃ የሚከበረው መልካ አቴቴ ሲሆን ይህን በተሳካ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁ በውይይቱ ወቅት ተገልጿል። በዓሉ ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ እንዲከበር ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ሲሉ አባ ገዳ ጎባና ሆላ ኢሬሶ በዚሁ ወቅት ተናግረዋል። ከተለያዩ ብሔር፣ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ጋር በመሆን በሰላም፣ በፍቅር፣ የህዝቡን አንድነት በሚያጠናክርና የኦሮሞ ባህልን በጠበቀ መልኩ ማክበር ያስፈልጋል ነው ያሉት።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም