ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የበካይ ጋዝ ልቀት ቅነሳ ግዢ ስምምነት ከዓለም ባንክ ጋር ተፈራረመች

501

አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 2/2015 ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የበካይ ጋዝ ልቀት ቅነሳ ግዢ የስምምነት ሰነድ ከዓለም ባንክ ጋር መፈራረሟን የፋይናንስ ሚኒስቴር ገልጿል።

የበካይ ጋዝ ቅነሳ ግዢ ማዕቀፍ የደን መመናመንንና በረሃማነትን በመቀነስ ቀጣይነት ያለው የደን ክብካቤን ለማረጋገጥ ያለመ ፕሮግራም ነው።

May be an image of 6 people and people standing

ለማዕቀፉ ሁለት ምዕራፎች ትግበራ እስከ 40 ሚሊየን ዶላር የሚደርስ ድጋፍ እንደሚደረግ የተመላከተ ሲሆን ይህም ተግባር ተኮር የደን ጥበቃን እንዲሁም ሌሎች ከከባቢ አየር ጋር ሊላመዱ የሚችሉ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ያካትታል።

በዛሬው እለትም ለመጀመሪያው ምዕራፍ የፕሮግራሙ ትግበራ የሚውል የ15 ሚሊየን ዶላር ስምምነት ነው የተፈረመው።

ሥምምነቱ በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ እና በምስራቅ አፍሪካ የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን መካከል መደረጉን ከገንዘብ ሚኒስቴር ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም