በሁለተኛው ከተማ አቀፍ ባዛርና ኤግዚቢሽን ከ170 በላይ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ይሳተፋሉ

204

አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 1/2015 ከነገ ጀምሮ ለሚካሄደው ሁለተኛው ከተማ አቀፍ ባዛርና ኤግዚቢሽን ከ170 በላይ የኅብረት ሥራ ማኅበራት እንደሚሳተፉ የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን አስታወቀ።

ከየካቲት 2 እስከ 6 ቀን 2015 ዓ.ም በኤግዚቢሽን ማዕከል የሚካሄደውን ሁለተኛው ከተማ አቀፍ የኀብረት ሥራ ባዛርና ኤግዚቢሽንን በማስመልከት በዛሬው እለት ሲምፖዚየም ተካሂዷል።

May be an image of 1 person, sitting and standing

በባዛርና ኤግዚቢሽኑ ከ170 በላይ የኅብረት ሥራ ማኅበራት የሚሳተፉ ሲሆን፤ ምርትና አገልግሎት እንዲሁም ተሞክሯቸውን የሚያቀርቡ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አብዲ ሙመድ፤ የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነትን ለማርገብ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሚና የማይተካ መሆኑን ተናግረዋል።

በሁለተኛው ከተማ አቀፍ የኀብረት ሥራ ኤግዚቢሽንና ባዛርም የግብርና ምርቶችን ዋጋ ለማረጋጋት ለሚደረገው ጥረት አጋዥ መሆኑን ገልጸዋል።

May be an image of 1 person and standing

የአዲስ አበባ የኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ዓሊ፤ የኅብረት ሥራ ማኅበራት የግብይት ድርሻን በማሳደግ ፍትሃዊ የግብይት ሥርዓት እንዲዳብር እየተሰራ ነው ብለዋል።

የእሑድ ገበያ ማዕከላትን አማራጭ የግብይት መዳረሻ በማድረግ በመዲናዋ በ133 ሥፍራዎች ግብይት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

በስድስት ወራት በሁሉም አካባቢዎች በተደረገው ግብይት ከ746 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ግብይት ተደርጓል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም