የሀረሪ ክልል አስተዳደር ምክር ቤት የሴክተር መስሪያ ቤቶችን የ6 ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ጀመረ

176

ሐረር (ኢዜአ) ጥር 30/2015 የሐረሪ ክልል የመሥተዳድር ምክር ቤት የክልሉን የሴክተር መስሪያ ቤቶች የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም መገምገም ጀምሯል።

በመድረኩ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንደገለፁት በግማሽ ዓመቱ ለማከናወን የታቀዱ ስራዎች በተለይም የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ፣ ነባርና አዳዲስ ፕሮጀክቶች ሂደት ያሉበት ደረጃ በትኩረት ይገመገማሉ ብለዋል።

የክልሉ የ6 ወራት ስራ አፈፃፀም ሪፖርት በክልሉ ፕላን ኮሚሽን የቀረበ ሲሆን በቀረበው ሪፖርት ላይ ውይይት ተደርጎ አቅጣጫ እንደሚቀመጥበትም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም