መገናኛ ብዙኃን በ36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የኢትዮጵያን ገፅታ እና ፓን አፍሪካኒዝም በማጉላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ

185

አዲስ አበባ ( ኢዜአ) ጥር 27 ቀን 2015 የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት በ36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የኢትዮጵያን ገፅታ እና ፓን አፍሪካኒዝም በማጉላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ።

36ኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 42ኛውን የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባን አስመልክቶ የሚዲያ ኮሚቴ የተለያዩ ባለ ድርሻ አካላትን በመጋበዝ ከመገናኛ ብዙኃን የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።

May be an image of 7 people, people standing, people sitting and indoor

ውይይቱ የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች በቅድመ ጉባዔ ፣ጉባዔ እና ድህረ ጉባዔ ወቅት በሚያከናውኗቸው የሥራ ስምሪቶች ላይ ሊከተሏቸው የሚገቡ አሰራሮች እና የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዙሪያ ላይ ያተኮረ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል የፕሮቶኮል ጉዳይ ዋና ሹም አቶ መክብብ ነጋሽ የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች የአገራቸውን የገፅታ ግንባታ በማጉላት የዜጋ ዲፕሎማትነታቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጠይቀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ ምክትል ቃል አቀባይ አቶ ሰላም ሙሉጌታ በበኩላቸው ጉባዔው ኢትዮጵያ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት በዘላቂነት ያስቆመ ስምምነት አድርጋ እየተገበረች ባለበት ወቅት መሆኑ የተለየ ገፅታ እንዲኖረው አድሮጎታል ብለዋል።

የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ሽፋን በሚሰጧቸው ዘገባዎች ላይ ይህን ስኬት መሠረት ባደረገ እና ሌሎች የፓን አፍሪካኒዝም እሳቤዎች እና የጉባዔው መሪ ቃል በሆነው አህጉራዊ ነፃ ንግድ ትስስርን ማፋጠን ላይ ከቅድመ ጉባዔ እስከ ድህረ ጉባዔ ድረስ ትኩረት እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም