የብልፅግና ፓርቲን ወክለው የተመረጡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትና የፓርቲው ዋና ፅህፈት ቤት አመራሮች በመንግስት የስድስት ወር አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት እያደረጉ ነው

244

ጥር 27 / 2015 (ኢዜአ) የብልፅግና ፓርቲን ወክለው የተመረጡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትና የፓርቲው ዋና ፅህፈት ቤት አመራሮች በመንግስት የስድስት ወር አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት ማድረግ ጀምረዋል።

መድረኩን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ያስጀመሩት ሲሆን ውይይቱ ፓርቲው በምርጫ ወቅት በማንፌስቶው ያስቀመጣቸውና ለሕዝብ ቃል የገባቸው ጉዳዮች አፈፃፀም ያሉበትን ደረጃ በመለየት በቀጣይ አፈፃፀሙን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ውጤታማ የክትትልና ድጋፍ ሥራ ለመስራት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ያግዛል ተብሏል።

የመንግስት የ2015 ዓ.ም የስድስት ወር አፈፃፀም ሪፖርት በኘላንና ልማት ሚኒስትሯ ዶክተር ፍፁም አሰፋ እየቀረበ ይገኛል።

በውይይቱ ባለፉት ስድስት ወራት በተከናወኑ ተግባራት ላይ ዝርዝር ውይይት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም