ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በእጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ በድል ጉዞው ቀጥሏል

167

አዲስ አበባ(ኢዜአ) ጥር 26/2015 ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ።

በፕሪሚየር ሊጉ የሰባተኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታዎች ትናንት በድሬዳዋ ተካሄደዋል።

የሊጉ መሪ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኦሜድላን 30 ለ 26 አሸንፏል።

ውጤቱን ተከትሎ ነጥቡን ወደ 14 ከፍ ያደረገ ሲሆን እስከ አሁን በሊጉ ያደረጋቸውን ሰባት ጨዋታዎች በማሸነፍ በአስደናቂ ግስጋሴው ቀጥሏል።

በሌላ ጨዋታ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ከምባታ ዱራሜን 28 ለ 24 ነጥቡን ወደ ሰባት ከፍ በማድረግ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የእጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ከአምስተኛ እስከ ዘጠነኛ ሳምንት ጨዋታዎች በድሬዳዋ ከተማ እንደሚካሄዱ የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን ማሳወቁ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት ውድድሩ እስከ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም