በቻን ውድድር ማዳጋስካር ከኒጀር የደረጃ ጨዋታ ያደርጋሉ

118

አዲስ አበባ(ኢዜአ) ጥር 26 /2015 በሰባተኛው የአፍሪካ አገራት ሻምፒዮና (ቻን ) ማዳጋስካር ከኒጀር ዛሬ የደረጃ ጨዋታ ያደርጋሉ።

በአልጄሪያ አስተናጋጅነት ከጥር 5 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የቻን ውድድር ነገ ይጠናቀቃል።

ማዳጋስካር እና ኒጀር ዛሬ ከምሽቱ 4 ሰአት ሚሉድ ሀዴፊ ስታዲየም ሶስተኛ ደረጃን ለማግኘት ይጫወታሉ።

በመጀመሪያ የቻን ተሳትፎዋ ጥሩ የሚባል ግስጋሴ ያደረገችው ማዳጋስካር በግማሽ ፍጻሜ በሴኔጋል 1 ለ 0 መሸነፏ የሚታወስ ነው።

የምዕራብ አፍሪካዋ አገር ኒጀር በግማሽ ፍጻሜው በውድድሩ አስተናጋጅ አገር አልጄሪያ 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ተሸንፋለች።

በተያያዘም የቻን ውድድር ነገ ይጠናቀቃል።

አልጄሪያ እና ሴኔጋል ከምሽቱ 4 ሰአት ከ30 በኔልሰን ማንዴላ ስታዲየም ዋንጫውን ለማንሳት ይፋለማሉ።

የቻን ውድድር በአገር ውስጥ ሊግ የሚገኙ ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበት ውድድር መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም