ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አልሸባብን ለመዋጋት የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ አባል ከሆኑ የመከላከያ ሰራዊት የጦር መኮኖች ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አልሸባብን ለመዋጋት የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ አባል ከሆኑ የመከላከያ ሰራዊት የጦር መኮኖች ጋር ተወያዩ
102
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 24/2015 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አልሸባብን ለመዋጋት የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ አባል ከሆኑ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የጦር መኮንኖች ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል።
የመከላከያ ሰራዊት አባላቱ አልሸባብን ለማጥፋት በአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪነት ተልዕኮን ወስደው የሚሰሩ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቲውተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “አልሸባብን ለመዋጋት የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ አባል ከሆኑት የመከላከያ ኃይላችን የጦር መኮንኖች ስለሚደረገው የመከላከል ጥረት ገለጻ ተደርጎልኛል“ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በምስራቅ አፍሪካ አልሸባብን የመዋጋት ዘመቻን ለማጠናከር በሶማሊያ በሚካሄደው ቀጣናዊ መድረክ ለመሳተፍ ዛሬ ሞቃዲሾ መግባታቸው ይታወሳል ፡፡