አምባሳደር ስለሺ በቀለ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር ተወያዩ

119

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 24/2015 በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ የሰላም ስምምነቱን ትግበራ ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር መወያየታቸው ተገለጸ።

አምባሳደር ስለሺ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ ጋር የሰላም ስምምነቱን ትግበራ እና ሂደት እንዲሁም የማህበራዊና ኢኮኖሚ ልማት ጨምሮ ሌሎችም ጉዳየች ላይ ያተኮረ ውይይት ማድረጋቸውን በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

May be an image of 4 people and people sitting

በሌላ በኩል ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ አምባሳደር ማይክ ሀመር ጋርም መነጋገራቸውን አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም