ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዴንቨር ከተማ በከንቲባ ሚካኤል ቢ ሐንኮክ ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያዩ

285

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 22 / 2015 የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዴንቨር ከተማ ከንቲባ ሚካኤል ቢ ሐንኮክ ከተመራ የልዑካን ጋር መወያየታቸው ተገለጸ፡፡

ከንቲባ አዳነች በዴንቨር ከተማ ከንቲባ ሚካኤል ቢ ሐንኮክ ለተመራ የልዑካን በከንቲባ ጽህፈትቤት የአስተዳደሩ የካቢኔ አባላት በተገኙበት አቀባበል መደረጉን የከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዴንቨር አዲስ አበባ በጀመረው አዲስ የበረራ መስመር የሁለቱን ከተሞች ግንኙነት ለማጠናከር ወደ አዲስ አበባ የመጣው ልዑክ ከከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ጋር መወያየቱንም ተገልጿል፡፡

በዚህም የሁለቱን ከተሞች ግንኙነት የሚያጠናክር ፍሬያማ ውይይት መደረጉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጠቅሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም