ኢትዮ ቴሌኮም አዳዲስ አገልግሎቶችን ይፋ አደረገ

376

አዲስ አበባ(ኢዜአ) ጥር 22/2015 ኢትዮ ቴሌኮም የደንበኞችን ችግር የሚፈቱ እና ሕይወትን ቀላል ያደርጋሉ ያላቸውን ሶስት አዳዲስ አገልግሎቶች ዛሬ ይፋ አድርጓል።

አገልግሎቶቹ ‘ቴሌ ድራይቭ’፣ ‘እልፍ ፕላስ’ እና’ ክላውድ ሶሉሽን’ ይሰኛሉ።

በአገልግሎቱ ይፋ ማድረጊያ ስነ ስርዓት ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩን ጨምሮ የኢትዮ ቴሌኮም ማኔጅመንት አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ቴሌ ድራይቨ ደንበኞች መረጃዎቻቸውን ለማስቀመጥ የሚያገለግል ልክ እንደ ‘ጎግል ድራይቭ’ አይነት መረጃ ማስቀመጫ ሲሆን እልፍ ፕላስ ደግሞ ለሙዚቃ ወዳጆች የተዘጋጀ ሙዚቃ በቀጥታ መከታተል የሚያስችል አማራጭ እንደሆነ ተገልጿል።

ክላውድ ሶሊሽን ደግሞ ሲስተሞችና ሶፍትዌሮችን ለማስቀመጥ የሚያስችል አገልግሎት መሆኑን ነው ኢትዮ ቴሌኮም ያስታወቀው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም