በጀርመን ካርልስሩህ በተካሄደ የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች በ3 ሺህ ሜትር በሁለቱም ጾታዎች አሸነፉ

118

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 20/2015 በጀርመን ትናንት ካርልስሩህ በተካሄደ የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች በ3 ሺህ ሜትር በሁለቱም ጾታዎች አሸናፊ ሆነዋል።

በሴቶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ አምስት ተከታትለው በመግባት የበላይነቱን ይዘዋል።

አትሌት ለምለም ኃይሉ 8 ደቂቃ ከ37 ሴኮንድ ከ55 ማይክሮ ሴኮንድ አሸንፋለች።

አትሌት ወርቁውሃ ጌታቸው 8 ደቂቃ ከ37 ሴኮንድ ከ98 ማይክሮ ሴኮንድ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ዳዊት ስዩም 8 ደቂቃ ከ39 ሴኮንድ ከ20 ማይክሮ ሴኮንድ ሶስተኛ ወጥተዋል።

አትሌት ሚዛን ዓለም እና አትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ አራተኛና አምስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

በወንዶች 3 ሺህ ሜትር አትሌት አብዲሳ ፈይሳ በ7 ደቂቃ ከ40 ሴኮንድ ከ35 ማይክሮ ሴኮንድ አሸናፊ ሲሆን በርቀቱም የቦታውን ክብረ ወሰን አሻሽሏል።

ቤልጂየማዊው አትሌት ሮቢን ሄንድሪክስ 7 ደቂቃ ከ40 ሴኮንድ ከ53 ሴኮንድ ሁለተኛ ሲወጣ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት አዲሱ ግርማ 7 ደቂቃ ከ41 ሴኮንድ ከ53 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

የጀርመን ካርልስሩህ የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር የዓለም አትሌቲክስ እ.አ.አ በ2023 እውቅና ከሰጣቸው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድሮች አንዱ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም