በወቅታዊ ጉዳይ ላይ እየተካሔደ ያለው ውይይት የሀገሪቱን ልማትና ሰላም ለማፅናት የጎላ ሚና አለው--ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ

142

ሐረር (ኢዜአ) ጥር 20 ቀን 2015 በወቅታዊ ጉዳይ ላይ እየተካሔደ ያለው ህዝባዊ ውይይት የክልሉን ብሎም የሀገሪቱን ልማትና ሰላም ለማፅናት ፋይዳው የጎላ መሆኑን የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለጹ።

"ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለብልፅግና ጉዛችን ስኬት" በሚል መሪ ሀሳብ በሐረሪ ክልል ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው።

በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት ርዕሰ መስተዳድሩ ፤ የውይይቱ ተሳታፊዎች የነቃ ተሳትፍ በማድረግ የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት መወጣት እንዳለባቸው አመልክተዋል።

የክልሉ ብሎም የሀገሪቱን ልማትና ሰላም ለማፅናት የውይይት መድረኩ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።

በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳይ እየተካሄደ ባለው ህዝባዊ ውይይት ላይ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ ከክልሉ ዘጠኙም የገጠርና የከተማ ወረዳዎች የተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም