ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋምቤላ ከተማ ገቡ

100
ጋምቤላ ግንቦት12/2010  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በጋምቤላ ክልል ይፋዊ ገብኝት ለማድረግ ጋምቤላ ከተማ ገቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋምቤላ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የተቀበሏቸው ሲሆን ወደ ጋምቤላ ከተማ ሲገቡም ህዝቡ በጎዳናዎች ላይ በመውጣት ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል። ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት በሚኖራቸው ቆይታ ከክልሉ ህዝብ ጋር በልማት በመልካም አስተዳደርና በሌሎች አጠቃላይ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። በተጨማሪም ዛሬ በከተማው ህዳር 29 አዳራሽ ከህዝብ ጋር ውይይት የሚያደርጉ ሲሆን ነገ ደግሞ በጋምቤላ ስታዲየም በመገኘት መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ከወጣው የድርጊት መርሃ-ግብር ለማወቅ ተችሏል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም