የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር የአምስተኛ ሳምንት መርሐግብር የመጨረሻ ቀን ውሎ

190

አዲስ አበባ(ኢዜአ) ጥር 19/2015 በኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎች  ኦሜድላ እና መቻል ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል።

የፕሪሚየር ሊጉ ውድድር ትናንት ከእረፍት መልስ በድሬዳዋ ከተማ መጀመሩ ይታወቃል።

ዛሬም የሊጉ መርሐግብር ቀጥሎ ሲውል የአምስተኛ ሳምንት ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል።

በዚሁ መሰረት ኦሜድላ መቻልን 41 ለ 32 ሲረታ መቻል ፋሲል ከነማን 37 ለ 22 አሸንፏል።

በተያያዘም ትናንት በተደረጉ የአምስተኛ ሳምንት የመክፈቻ ጨዋታዎች  ቂርቆስ ክፍለ ከተማ 39 ለ 19 በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናክሯል።

በሌላ ጨዋታ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ፌደራል ማረሚያን 24 ለ 18 ረቷል።

የሰባተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከአንድ ቀን እረፍት በኋላ የፊታችን እሀድ እና ሰኞ ይካሄዳሉ።

ከአምስተኛ እስከ ዘጠነኛ ሳምንት የሊጉ መርሐግብር በድሬዳዋ ከተማ እንደሚከናወን የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

በቀጣዩ ወር የካቲት 1 የፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ዙር ውድድር እንደሚጠናቀቅም አመልክቷል።

የእጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ከአንደኛ እስከ አራተኛ ሳምንት ጨዋታዎች በታህሳስ ወር 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ መካሄዱ የሚታወስ ነው።

የፕሪሚየር ሊጉን ሰንጠረዥ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በ10 ነጥብ ይመራል።

መቻል በስምንት እንዲሁም ኦሜድላ በስድስት ነጥብ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

ሚዛን አማን ከተማ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን ዘጠነኛ ደረጃ ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም