የዓለም አቀፉ የትምህርት አጋርነት ድርጅት የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፉ ለመደገፍ ዝግጁ ነው

167

ጥር 18/2015 (ኢዜአ) የዓለም አቀፉ የትምህርት አጋርነት ድርጅት የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፉ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዓለም አቀፍ የትምህርት አጋርነት ድርጅት ዋና ስራ አሰፈጻሚ ላውራ ፍረጀንት ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ፕሮፌሰር ብርሃኑ በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተደረጉ ለውጦችን እና እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን አብራርተዋል።

የትምህርት ጥራትንና ፍትሀዊነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንና ጥራት ያለው ትምህርት ለዜጎች ለማድረስ እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።

ሚኒስትሩ የዓለም አቀፍ የትምህርት አጋርነት በኢትዮጵያ በትምህርት መስክ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ጠቁመው አሁንም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡

የዓለም አቀፍ የትምህርት አጋርነት ዋና ስራ አስፈጻሚ ላውራ ፍረጀንት በበኩላቸው በኢትዮጵያ በትምህርት ተደራሽነት የተከናወኑ ተግባራት አመርቂ ውጤት ተገኝቶባቸዋል ገልፀዋል፡፡

ድርጅታቸውም የኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፉ ለመደገፍ ከአለም አቀፍ ለጋሾች ጋር በመወያየት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም